ይህ በትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፤
ዞን ኣመራሮች፤ ሞያተኞች፤ የኦዲት ባለሞያዎች፤ የስርኣቱ ኣባላትና የህዝብ ተወካዮች የተገኙበት ስብሰባ ስለ ሙስና የሚመልከት
ሁኖ ከህዳር 23-24/ 2006 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተካሂደዋል፣
በተደረገው ስብሰባ ከፍተኛ የስርአቱ ልኡክ ሁኖው ስብሰባውን የመሩት ኩማ ደመቅሳና
ኣባይ ወልዱ ሲሆኑ፣ ተሰብሳቢው ህዝብ እንደዋናው አርእስት ያነሱት
ሙሱና የሚመለከት ጉዳይ በእዉነት ሊስተካከል ከተፈለገ በመጀመርያ መድረኩን የሚመሩ ሰዎች ራሳቸው የፀዱ መሆን አለባቸው አሁን ግን
የምንናገርው ጉዳይ የለንም በማለት ኢ-ፍትሓዊ ለሆነው አሰራር እንደተቃወሙት ከተሳታፊዎቹ የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
መረጃው አክሎ እንደገለጠው ተሰብሳቢዎቹ ካቀረቡት ሃሳብ ከላይ እስከታች
ያላቹህ የህወሓት ኢህአዴግ አማራሮች በሙስና የተዘፈቃቹ በመሆናቹሁ ስለ ሙሱና የሚናገራቹሁ ሰው ልክ እንደ እንቆቆ እሬት እንደ
ሚመራቹ እየታዘብን ስለሆነ፣ እያወቅንን እንዳላወቅንን ሁነን ቆይተናል፣፣
አሁንም የነበራቹ
ህመም ከአእምሮአቹሁ አፅድታቹሁ ህዝብ ያቀረበላቹሁን እዉነተኛ ሂስ
ተቀብላቹሁ ለመታረም ወስናቹሃል የሚል እምነት ስለሌለን ሌላ ገለልተኛ ሰዉ መጥቶ እናንተ እነደ
ተራ ሰው ሁናቹ የምትገመገሙበት መድረክ ይፈጠር ብለው መናገራቸው የደረሰን መረጃ አክሎ አስታወቀ፣፣
ተሰብሳቢዎቹ በሙሱና ተዘፍቀዋል ብለው ከጠቀስዋቸው የስርኣቱ ባለስልጣናት
መካከል፣ ራሱ ስብሰባው እየመራ የነበረው ኣባይ ወልዱ፣ ተድሮስ ሓጎስ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ጌታቸው አስፋው እንዲሁም ኪሮስ ቢተው
3.4 ሚልዮን ብር የሚደርስ የሃገርና የህዝብ ገንዘብ የመዘበሩ ሲሆኑ እንዲሁም ሚኪኤለ ኣብራሃ የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስተዳዳሪ
የነበረ በሙሱና ኣማርሮ ህዝብ ከተናገረ በሃላ ወደ ማእከላዊ ዞን
የተዛወረ 1.8 ሚልዮን ብር የበሉ እንደሆኑ፣ ራሱ ኩማ ደመቅሳ ቢሆንም በሙሱና ከተዘፈቁ የስርኣቱ ከፍተኛ ባለስልጣን መሆኑ ብግልፅ
በመድረኩ እንደቀረበለት እና ስብሰባው ያለ ውጤት እንደተጠናቀቀ ከአክሱም ከተማ የደረሰን መረጃ አመልክተዋል፣