Sunday, December 8, 2013

ሚዛናዊ የሆነ የመኣርግ አሰጣት መኖር አለበት በማለት ተቃዉማቸዉን ያሰሙ የመከላከያ ሰራዊት መኮነኖች ብድብቅ እየተገደሉ እና እየተሰወሩ እንዳሉ ከመከላከያ ሰራዊቱ የፈተለከ መረጃ ኣስታወቀ፣




በምእራባዊ ዞን 43ኛ ክፍለ ጦር የሚገኙ የሰራዊቱ አመራሮች “እየተሰጠ ያለዉ ማኣርግ ሚዛናዉነት የለዉም፣ የመአርግ መመዘኛ ምንድነው ይነገረን? በአገልግሎትና የስራ ዉጤት ብሆን ኑሮ ተመሳሳይ የሰራ ተመክሮና ተሳትፎ ያለን የሰራዊቱ አባሎች ልዩነት ኣይፈጥርብንም ነበር፣ ሊረዳንም ኣልቻለም ይሄንን ሳናዉቅ የሆነ ስራ ለመስራት ፍቃደኞች ኣይደለንም፣” ላሉ በለሊት እንቅስቃስያቸው በመከታተል ከመኝታ ቤታቸው እየለቀሙ እንደወሰድዋቸና የት እንደገቡ እንደማይታወቁ የደረሰን መረጃ ገልጠዋል፣
    ለነዚህ በየግዜው እየተከታተሉ ሲያጠፉዋቸው የቆዩ የሰራዊቱ መኮኖኖች ሰራዊቱ እንዳያዉቃቸው ፈርተው በስብሰባው ላይ እከሌ ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሄደ ወደ ዘመዶቹ ሄደ፤ ከዳ፤ ገንዘብ በልቶ እንዳይያዝ ሸሸ እያሉ ለፀረ ህዝብ ተግባራቸው መሽፈኛ እየተጠቀሙበት የቆዩ እንኳ ቢሆኑ፣ ኮለኔል ካሳሁን የተባለ ለትግራይ ተወላጆች መአርግ እየሰጣቹ ነው ለኔም ይመለከተኛል ብሎ በስብሰባው ላይ ከተናገረ በኋላ በድብቅ አፍነው ከወስደውት በኋላ ለማታው ጠፍቷል ብለው በመናገር በድብቅ ለአራት ወር ገደማ አስርው ሲያሳቃዩት ከቆዩ በሃላ ህዳር 21/ 2006 ዓ.ም ተፈቶ ወደ ክፍለጦሩ ከተቀላቀለ በኋላ በራሱ ላይ በደረሰው እና በሌሎች የመከላክያ ሰራዊቱ እስሮኞች እየተፈፀመ ያለውን ምስጢራዊ ተግባር እንዳያጋልጥ ስለ ሰጉ በመጣበት ቀን ወዲያውኑ ታመዋል በማለት እንደገደሉት ለማወቅ ተችለዋል፣