በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ዞን በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ከተለያዩ ተቋማት በድግሪና በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ጨርሰው የተመረቁ ወጣቶች። በስራ እጦት ምክንያት የቤተሰቦቻቸውና
የሃገር ሸክም ሆነው እንዳሉና። በኮብልስቶን ስራ ትሰማራላቹህ ተብሎው ከተመዘገቡ በሃላም። የከተማዋ አስተዳዳሪዎች የተደበቀ ኣጀንዳቸውን
ለመተግበር ሲሉ ከስልጠናው ጋር የማይሄድ ፈተና በመስጠት ተማሪዎቹ እንዲወድቁ በማድረጋቸውና። አድልዎ የተጠናወተው ኣሰራር በመከተላቸው።
ተማሪዎቹ ባለፈው ሳምንት ያነሱትን ተቃውሞ አሁንም አጠናክረው እየቀጠሉበት መሆኑ ታውቀዋል፣
መረጃው አክሎ እንደገለፀው። እነዚህ ትምህርታቸውን
ጨርሰው ግዝያቸውን በከንቱ እያሳለፉት ያሉ ተማሪዎች። በድንጋይ ምንጣፍ ስራ /በከብልስቶን/ ተሰማርተው እለታዊ ኑሮኣቸውን እንኳ እንዳይገፉ። በከተማው የሚገኙ የስርኣቱ ካድሬዎችና ኣስተዳዳሪዎች ለራሳቸው በሚጠቅም መንገድ
ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት በመሆናቸው። ጉዳዩ መፍትሄ እስኪያገኝ በማለት። ህዳር 27/ 2003 ዓ.ም ያነሱትን ተቃውሞ ኣጠናክሮው
እየቀጠሉበት መሆኑን። ከአካባቢው ከተገኘው መረጃ ሊታወቅ ተችለዋል፣