Wednesday, December 11, 2013

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ባንኮች። ባለስልጣናት የመንግስት ሰራተኞች በሚወስዱት ብድር ምክንያት። ኪሳራ ውስጥ እንደወደቁ። ምንጮቻችን ከተለያዩ የክልሉ ኣካባቢዎች አስታወቁ፣




በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት የመንግስት ሰራተኞች። ከተለያዩ ባንኮች በብድር የወሰዱት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ። በተሰጣቸው የግዜ ገደብ መሰረት ሊመልሱት ባለመቻላቸውና። ባንኮቹ ሊወጡት ወደማይችሉበት ኪሳራ ውስጥ በመዘፈቃቸው። ከአሁን ወድያ ለማንኛውም ባለስልጣንና የመንግስት ሰራተኛ ብድር እንዳይሰጥ መወሰኑ። በባንኮቹ ከሚሰሩ ሰራተኞች አፈትልኮ  በደረሰን  መረጃ ሊታወቅ ተችለዋል፣
     በመጨረሻ መረጃው እንዳስታወቀው። ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ ከባንክ ለተበደረው ገንዘብ በተቀመጠለት የግዜ ገደብ ሳይመልስ ሲቀር። ንብረቱና ድርጅቱ ተሽጦ ወደ ባንክ ገቢ  ለመድረግ ባንኮቹ ምንም እንከን ገጥሟቸው አያውቅም ነበር፣ የስርአቱ ባለስልጣናት የተበደሩት ገንዘብ ለማስመለስ ሲባል። ንብረታቸው በሃራጅ መልክ እንዲሸጥና ወደ ፍርድ በማቅረብ ረገድ ተገቢ ውሳኔ የሚሰጥ ኣካል ባለመኖሩና በሌላው የሕብረተሰብ ክፍል ላይ ያስፈፀሙት ስራ  መተግበር አቅቶአቸው። ባንኮቹ በትልቅ ኪሳራ ውስጥ እንዲወድቁ ምክንያት ሆነዋል ሲል መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣