Sunday, December 22, 2013

በከፋ ዞን። ጫና ወረዳ፤ ዋቻ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በመሰረተ ልማት እጥረት ማህበራዊ ኑሮኣቸው ለመምራት ተቸግረው እንዳሉ ያገኘነው መረጃ አስታወቀ፣



በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ከፋ ዞን፤ ጫና ወረዳ ውስጥ የሚኖር በርከት ያለ ህዝብ። ስር የሰደደ የመሰረተ ልማት ችግር እንዳለውና። ይህን ከእለታዊ ኑሮኣቸው በቀጥታ ተያያዥነት ያለው የመሰረተ ልማት እጥረት በቀዳሚነት ታይቶ መፍትሄ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረኮች እንደገለፁና ለሚመለከታቸው አካላት ቢያመለክቱም። ሰሚ  እንዳላገኙ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣
    በቀዳምነት ታይቶ መፍትሄ እንዲደረግላቸው ከተጠየቅዋቸው መሰረተ ልማቶች መካከል። የመብራት ሃይል ዝርጋታ፤ የሚጠጣ ንፁህ ውሃና የመሳሰሉት ትኩረት ተሰጥቶበት ባለመሰራቱ። በከፋ ችግር ላይ ወድቆው የሚገኙ የዋቻ ኣካባቢ ነዋሪዎች። በእለታዊ ሂወታቸው መሰናክል ሆኖ ላለው ችግር በአስተዳዳሪዎቹ እንዲፈታላቸው በማለት የህዝቡን ብሶት ለማድረስ ወደ ወረዳው ጽ/ቤት ሃላፊው ደምሴ የሄደው አቶ ቃቆ ወልደ ገብርኤል ለተባለው ወገን ተቀብሎው በማሰር ደብዛውን ስላጠፉት። ህዝቡ የተጠየቀው ጥያቄ ባለመመለሱና የህዝቡን ተወካይ ለሆነው ግለሰብ ይዘው ስላጠፉት። የት አደረሳችሁት በማለት ተቃውማቸው በማሰማት ላይ መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታው አክለው አስረድተዋል፣