Sunday, December 22, 2013

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል። አሶሳ ከተማ ውስጥ። በፀረ ሽምቅ ስም የተሰማሩ የስርአቱ ታጣቂዎች። ሴቶችን አስገድደው በመድፈር ሥራ ላይ በመጠመዳቸው። ነዋሪዎቹ ምሬታቸው እያሰሙ መሆናቸው ተገለፀ፣



በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ፤ ሎጂጋንፎ ወረዳና ሶኒ ከተማ የሚኖሩ ባለ ሆቴል፤  መጠጥ ቤትና  ባለ ሱቅ ቤቶች የሆኑ ሴቶች። ፀረ ሽምቅ በመባል የሚታወቁ የስርአቱ ታጣቂዎች በመሳርያ እያስፈራሩ። አስገድደው እየደፈርዋቸው መሆኑን ከስፍራው ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣ 
     በተመሳሳይ በደዴሳ ወንዝ አካባቢ በሚገኝ የእርሻ ልማት ውስጥ ተሰማርተው ከሚሰሩ ሴት ወገኖቻችን። በአንደዋ ላይ ታጣቂዎቹ በፈፀሙት አረሜናዊ የወሲብ ጥቃት ምክንያት። ለከባድ አካላዊ ችግር በመጋለጥዋ። ሆስፒታል ድረስ እንደሄደች የደረሰን መረጃ አስታውቀዋል፣
     የአሶሳና የሶኒ ከተማ ህዝብ በላያቸው ላይ እየደረሰባቸው ያለ ጭካኔ የተሞላበት የመብት ጥሰት እንዲቆም በማለት ታጣቂዎቹን ለሚመሩ የበላይ ኣዛዦች ብሶታቸው ቢያቀርቡም። ሁኔታውን አጣርተው ተገቢውን ቅጣት ከመስጠት ይልቅ። የኛ ሰራዊት በእንደዚህ አይነት ተግባር አይሰማራም በማለት አስፈራርተው እንደ መለስዋቸው መረጃው ጨምሮ አስገንዝበዋል፣