Sunday, December 22, 2013

በመቀሌ ከተማ አግባብነት በሌለው መንገድ የንግድ ድርጅታቸው ታሽጎባቸው የቆዩ ነጋዴዎች ለስርዓቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ እየተገደዱ እንዳሉ ምንጭታችን ከከተማዋ ገለፁ፣



ባለፈው ግዜ የገቢና የወጪ መቆጣጠርያ ሂሳብ የላችሁም ተብለው በመቀሌ ከተማ አስተዳደር ትዕዛዝ። ድርጅታቸው ተዘግቶ በከባድ ችግር ወድቀው አቤቱታቸዉን ሲያሰሙ የቆዩ ነጋዴዎች በአሁኑ ግዜ የከተማዋ አስተዳደር ድርጅታቹህ እንዲከፈት ከፈለጋችሁ ጥፋተኞች ነን ብላችሁ ለመንግስት  ይቅርታ ጠይቁ። አንልም ካላችሁ ግን አይከፈትም እንዳላቸው ተበዳዮች ለምንጮቻችን ከሰጡት መረጃ ለመረዳት ተችሏል፣
     መረጃው ጨምሮ። የመቀሌ ከተማ አስተዳደር በተለይ ደግሞ  የሓድነት ወረዳ አስተዳደር ድርጅታቸው ለታሸጉ ነጋዴዎች ሰብስቦ እናንተ የፈፀማችሁት ጥፋት ከባድ ቢሆንም መንግስታችን ይቅርታ ለጠየቀ ነጋዴ ተቋሙን የሚከፍትለት መሆኑን እያወቃቹህ። ለምንድነው ተሎ ብላችሁ ይቅርታ የማትጠይቁ እያለ በማስፈራራት። ተገደው እንዲጠይቁ ለማድረግ ላይና ታች በማለት በእኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችላል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዚሁ ድንገተኛ ትእዛዝ ያልተቀበላቹህ ተብለው በመቀሌ ከተማ የታሽጉ የንግድ ተቋማት እስከ 1000ሺ የሚደርሱ መሆናቸውና ከዚህ በፊት በነበረው የዜና ጥንቅራችን መግለፃችን ይታወቃል፣