Monday, December 23, 2013

በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ለሚኖር ህዝብ። አንድ ለአምስት በተባለው የስለያ መረብ የልተካተተ፤ ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አለው እያሉ ከህብረተሰቡ እየነጠሉት እንደሆነ ተገለፀ፣




     በአማራ ክልል አዊ ዞን  ጃዊ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ለሚኖር ህዝብ አንድ ለአምስት በተባለ አደረጃጀች ውስጥ ያልተካተተ ዜጋ እንደ ፀረ ልማትና የአባይ ግድብ እንደሚያደናቅፍ ስለሚታሰብ፣ በዚህ የስለያ መረብ ያልታቀፉ ሰዎች ሁኔታቸው በተቃላጥፈ ሁኔታ ወደ በላይ ሓላፊዎች ሪፖርት እንዲላክ፣ የወረዳዋ አስተዳዳሪ ኣቶ ኣየለ፣ ትዕዛዝ ማስተለለፉ ከወረዳዋ ያገኘነው መረጃ አመለከተ፣
    መረጃው ጨምሮ እንደሚያስረዳው፣ እነዚህ አንድ ለአምስት በሚል አደረጃጀት አንታቀፍም ያሉ ነዋሪዎች፣ ልክ እንደተቃዋሚ አባላትና ተላላኪ፣ አሸባሪ ተፈርጀው፣ ጥንቃቄ የተሞላው ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግባቸው፣ የወረዳዋ አስተዳዳሪ  ተጨማሪ ትእዛዝ እንደሰጠ፣ ሁኔታዉን እየተከታተሉ ያሉ ወገኖቻችን ከቦታው ገልፀዋል፣
     በዚህ አንድ ለአምስት በሚል የስለያ መረብ የገባ ዜጋ የት ዋልክ የት አደርክ  እየተባለ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገበት እንዳለና፣ በዚህ መሰረት ደግሞ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ ዕለታዊ ኑሮዉን መምራት እንደማይቻል የተረዱ የወረዳዋ ነዋሪዋች፣ ለዚህ አንድ ለአምስት የሚል አደረጃጀት እንዳልተቀበሉት የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል፣