የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው በአማራ
ክልል ሰሜንና ደቡብ ጎንደር የኑሮ ውድነት ከበፊቱ በእጥፍ መጨመሩ ሳያበቃ በርከት ያሉ እለታዊ ከህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር ትስስር
ያላቸው ከአካባቢው ጠቅልለው በመጥፋታቸው ህዝቡ እሮሮውን በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችልዋል፣
መረጃው በማስከተልም
በተለይ የጎንደር ከተማ ህዝብ አጋጥሞት ካለው የገባያ የዋጋ ንረት ዋነኛ ሰለባ ሁኖ እያለ ስርዓቱ በሚቆጣጠራቸው የማከፋፈያ ተቋማት
ለመግዛት በሚሄዱበት ግዜ የማንነት ካርድ ለቀበሌ እንዲያሳዩ ስለ ሚገደዱ የተወሰነ የግዥ ፍቃድ ሲሰጣቸውም እስከሚወስዱ ድረስ ታችና
ላይ እያሉ ተራ በመያዝ ግዜአቸውን ማባከን ግድ ሁኖባቸው እንደሚገኙና በተለይም የጥራጥሬ እህል አይነቶች እና የቅባት እህል አይነቶችን
ከአቅማቸው በላይ በሆነ ክፍያ እየገዙ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ገልፅዋል፣
ከጎንደር
ከተማ ሳንወጣ በከተማዋ እየታየ ያለው ተደጋጋሚ የመብራት መጥፋት ምክንያት ህዝቡ ተቸግሮ እንዳለና ከዚህ በፊት ሲያገለግሉ የቆዩ
ትራስፎርሞሮች ተነቅለው ወደሌላ ቦታ እየተወሰዱ በመሆናቸው ሳብያ፤ የጎንደር ህዝብ እተደረገ ላለው ሃላፊነት የጎደለው ተግባር አቤቱታውን
ቢያሰማም የሚሰማው አካል እንዳላገኘ ለማወቅ ተችልዋል፣