በመረጃው መሰረት በተለያዩ
የትግራይ ዞኖች ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚኖሩ ህዝቦች የህወሃት አባል ባለመሆናቸው ምንያት የማንነት ወረቀትና እንዲሁም በብድር መልክ
ከተለያዩ ተቋማት ገንዘብ እንዳይወስዱ ተከልክለው እንደሚገኙና ከአንድ
ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሰው ዕለታዊ ኑሮአቸውን መምራት እንዳይችሉ የተደርጉበት ሁኔታ እንዳለ። ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን
መረጃ አመለከተ።
መረጃው በማስከተል ማነኛውም የክልሉ ተወላጅ የማንነት ወረቀት ማውጣት የሚችለው
በአካባቢው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በኔት ዎርክ በሚመሩ የህወሃት ካድሬዎች አባል መሆኑ ተርጋግጦ የተፈረመበት ወረቀት ማምጣት ካልቻለ
የማንነት ወረቀት ይሁን ለሎች ጥቅማጥቅሞችን እንዳያገኝ የሚከለክል ህግ በክልሉ ባለስልጣናት ተነድፎ ስለሚገኝ በእነዚህ የህወሃት አባል ባልሆኑ ዜጎች ላይ ስነአይምሮአዊ
ቀውስ እያስከተለባቸው መሆኑ ተገልፅዋል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ የትግራይ ህዝብ 17 አመት ሙሉ ታግለን መተኪያ የሌለውን ሂወታችንና ንብረታችንን ገብረን ያገኘነውን ድል ተጠቅመው ወደ
ስልጣን የመጡት እነዚህ መሰሪ የህወሃት ባለስልጣናት ከደርግ የባሱ ጨቋኝ ሆኑብን በማለት በሚያገኝዋት አጋጣሚ ሁላ መነጋገርያ አጀንዳቸው
አድርገዋቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል።