በደረሰን ዘገባ መሰረት በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ በንግድ ስራ የሚተዳደሩ ዜጎች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን
ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምክንያት ለኪሳራ ተዳርገው ድርጅቶቻቸው ለመዝጋት ተገደዋል፣ ድርጅቶቻቸው ከዘጉት ነጋዴዎች መካከል።-
-አቶ አስፋው መንገሻ የእህል መጋዝን የነበራቸ
-አቶ አለልኝ ወንድ አፍራሽ
-መምህር ገዛኢ ማስረሻ የመኪና መለዋወጫ መደብር የነበራቸውና ሌሎችም ይገኙበታል፣
ግብር በማስከፈል ስራ የተስማሩት የመንግስት ሰራተኞችና ሃላፊዎች ጉቦ ለሚከፍላቸው ነጋዴዎችን ዝቅተኛ ግብር
የሚገቱላቸው ሲሆን በማይከፍሉ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ግብር ይጩኑባቸዋል ፣ ነጋዴዎቹ ፍትሃዊ የግብር አከፋፈል ስርዓት እንዲኖር
ለሚመለከተው አካል ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለማወቅ ተችሏል፣