Friday, February 28, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ የሚልሻ አባልት በዞኑ የትህዴን ወረቀት ተበትንዋል በሚል ጭንቀት በአካባቢው በጠንካራ ወታደራዊ ጥበቃ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት ከፍተኛ የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣናት የትህዴንን ድርጀት የሚያስተዋዉቁ ፍምፕሌቶች በምዕራብ አካባቢ ተበትነዋል የሚል ጭንቀት ስላደረባቸው በዞኑ የሚገኙ ለስርዓቱ ታማኝ የሆኑ የሚሊሻ አባላቶች የካቲት 11 እስከ ሚያልፍ ድረስ ሌት ተቀን ያለምንም እርፍት ጥበቃቸውን እንዲያጠናክሩ ትዕዛዝ አውርደዉባቸው ስለሚገኙ በዚህ የተነሳም እነዚህ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ታጣቂ ምልሻዎች በከባድ ጭንቀት ውስጥ ተዘፍቀው እንደሚገኙ በረጃው አመለከተ።
    መረጃው አክሎ የወያኔ ካድሬዎች የትህዴን ወረቀት ተበትንዋል እያሉ ለሚነዙት ወሬ እያወቁም ይሁን ባለማወቅ ለታጋይ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ለሚያደርጉት የዲሞክራሲ ትግል የምስራች እየነገርዋቸው እንዳሉ የገለፀው ይህ መረጃይህንን የሰማዉ የታጋይ ቤተሰብም ልጆቻችን እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳቸው እጅግ የሚያስደስት ነው ድምፃችሁ አይጥፋ እያለ ደስታውን በመግለጽ ላይ እንደሚገኝ ለማውቅ ተችላዋል።
    በዚህ መሰረት በትህዴን የትግል ስልትና ፈጣን ግስጋሴው የተደሰቱ ከሁሉም የሃገራችን አካባቢ የድጋፍ ደብዳቤዎች እየጎረፉ እንዳሉና የደብዳቤዎቹ ይዘትም ከትህዴን ጎን በመሰለፍ ትግሉ የሚጠይቀውን ሁሉ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልፅ እንደሆነና ድጋፉም ለትህዴን የትግል ጉዞ የሚያፋጥን ሲሆን ለጨቋኙ የህወሃት-ኢህአዴግ ስርዓት ደግሞ ውድቀት እንደሆነ ህዝቡ ከላካቸው መልእክቶች ለመረዳት ተችለዋል።