Monday, March 10, 2014

በአስገደ ፅንብላ ወረዳ ወስጥ የሚገኙ ንፁሃን ወገኖች የእርሻ መሬታቸው በመነጠቃቸውና ለፀረ ህዝቡ አሰራር በመቃወማቸው ምክንያት በስርአቱ ተላላኪዎች እየተገደሉ መሆናቸው ተገለጸ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ አስገደ ፅንብላ ወረዳ፤ ደብረ ማርያም ጣቢያ፤ ቀበሌ ደርሜላ ውስጥ የሚገኙ በህጋዊ መንገድ የእርሻ መሬት ተሰጥቶዋቸው ለአመታት ሲጠቀሙበት የቆዩ በህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች ተነጥቀው ባዶ እጃቸው ከቀሩት ነዋሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በሪሁ ሲሳይ ኑሮኣችን ምን ሰርተን እንምራው ብሎ በመቃወማቸው ምክንያት አቶ ኪሮስ ፀሃየ በተባለው የስርአቱ ተላላኪ በድንጋይ ተደብድቦ እንዲገደል መደረጉ ከቦታው በተገኘው መረጃ ሊታወቅ ተችለዋል።
    ይህ በሂወቱ ላይ ግድያ የተፈፀመበት ንፁህ ወገን በወረዳው አስተዳዳሪዎች የተፈፀመው ስርአት የጎደለው አሰራር ስለ ተቃወመና ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ጥያቄ በማንሳቱ ምክንያት ብቻ እንደሆነ። መረጃው አክሎ አስረድተዋል።