Monday, March 10, 2014

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች በህዝቡ ላይ ተደጋጋሚ የማደናገር ተግባር እየፈፀሙ መሆናቸው ከቦታው የተገኘ መረጃ አስታወቀ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የህወሃት ኢሀዴግ አስተዳዳሪዎች ቀደም ሲል ሃያ በሃያ በሚል የሚታወቀው መኖርያቤታቸው በሚመለከታቸው አካላት ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ለየካቲት 19/2006 ዓ/ም ወደ ከተማው ማዛጋጃቤት መሰብሰብያ አዳራሽ እንዲመጡ በስርአቱ ተላላኪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው በቦታው ቢገኙም የከተማው ከንቲባ አቶ ሚኪኤለ አባይ እኛ አልጠራናቹሁም ብሎ እንደመለሳቸው መረጃው አስታወቀ።
     ብከንቲባው ተግባርና በአጠቃላይ በስርአቱ እየደረሰባቸው ባለ ተደጋጋሚ የማደናገር ስራ የተቆጡ ከ300 በላይ የሆኑ ቤታቸው የፈረሰባቸው የቀድሞ ታጋዮች የሚገኙባቸው ነዋሪዎች ለስብሰባ ተጠርታቹሃል ተብሎው ከተማው ውስጥ ወደ ሚገኘው ማዛጋጃ ቤት የሄዱ ወገኖች ቀደም ሲል ያለ ምንም ካሳ ቤታችን ማፍረሳቹህ ሳይበቃ አሁንም ተሰብሰቡ ብላቹህ ስታበቁ የጠራቹህ ኣካል የለም እያላቹህ ከስራችን ማስተጓጎላቹህ በህዝቡ ላይ ያላቹህ ጣላቻና ንቀት የሚያሳይ ነው ረጅም ሳትጓዙ ዋጋ እንደሚያስከፍላቹህ ጥርጥር የለውም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሃለቃ በሪሁና አቶ ደመቀ የተባሉ የቀድሞ ታጋዮች የሚገኙባቸው ወገኖች በካድሬዎቹ ፊት ብሶታቸው እንደገለፁ ለማወቅ ተችለዋል።
    ይህ በንዲህ እንዳለ በወቅቱ ወደ ስብሰባው ከተጠሩት በቁጥር አንድ መቶ የሚሆኑ ያጋተማቸው ችግር አስመልክተው መፍትሄ እንዲያገኙ በማሰብ ወደ ዞኑ ባለስልጣኖች ቢሄዱም የፅ/ቤቱ ጥበቃዎች ጥያቄያቹህ የሚሰማ ኣካል የለም ገባር ሆቴል በተባለው ቦታ ስብሰባ ላይ ናቸው ብለው እንደመለስዋቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።