Thursday, June 19, 2014

የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው ወገኖች ተብሎ ከለጋሽ ሃገራትና ድርጅቶች የተገኘው የእርዳታ እህል የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት እየተጠቀመበት መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፣፣



ባለፉት ቅርብ ቀናት ባገራችን ሰሜናዊ ክፍል ለሚገኙ የተቸገሩ ወገኖች እንዲሰጥ ተብሎ፣ በመቐለ ከተማ “አዋሽ” ተብሎ በሚጠራው የእህል ማከማቻ መጋዝን የነበረውን እህል፣ ጨለማን ተገን በማድረግ በመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪ እየተጫነ “ሃይለ ወዲ አነንያ በተባለውና በሌሎች ወፍጮ ቤት” እየተፈጨ ለሰራዊቱ ምግብ እየዋለ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ከቦታው አስታወቁ፣፣    
     ስልጣን ላይ ያለው የወያኔ ስርአት በተቸገረ ወገን ስም ከለጋሽ አገሮች የሚመጣውን የእርዳታ እህልና ገንዘብ ከረጅም ግዜ ጀምሮ ለመዝናኛና ለሰራዊቱ ቀለብ እየተጠቀመበት እንደቆየ ይታወቃል፣፣