Thursday, June 19, 2014

በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን የፓዊ ወረዳ ነዋሪዎች በስርአቱ አመራሮች ከሚኖሩበት አካባቢ እየተፈናቀሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣፣በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ መንደር አምስት፣ ስምንትና ዘጠኝ እየተባሉ የሚጠሩትና ሌሎችም ስማቸው ባልተገለፁ ስምንት ቀበሌዎች ሲኖሩ የቆዩ ከ 9ሺ በላይ የሆኑ ዜጎቻችን ስኳር ፋብሪካ ለመትከል በሚል ምክንያት ያለ ምንም  ቅድመ ዝግጅነትና እገዛ በስርዓቱ አመራሮች እየተፈናቀሉ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል፣፣
    የኢህአዴግ አፋኝ ስርአት፣ ህዝቡን የማፈናቀል ሂደቱ ተግባር ላይ ለማዋል የፌደራል ፖሊሶችና ሌሎች ተጨማሪ ታጣቂዎች በማሰማራት፣ለነዋሪው ህዝብ አስገድደው ከሚኖሩበት ቦታ በማፈናቀል ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየበተኑት መሆናቸውን መረጃው አስረድቷል፣፣
    ይህ ህዝቡን የማፈናቀል ድርጊት ህዝባዊ ሃላፊነት የማይሰማው በሙስና የተጨማለቀውን የኢህአዴግ ስርአት ስልጣን ላይ እስካለ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ያካባቢው ህዝብም በድርጊቱ ተማሮ ብሶቱን እየገለፀ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣