Sunday, August 3, 2014

በአፋር ክልል ሃምሌ 21/2006/ዓ,ም ከአሳይታ ከተማ ወደ ሰመራ ሰው ጭና ትጓዝ የነበረች መኪና ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተመታ በመገልበጧ ምክንያት በውስጧ ተሳፍረው የነበሩ 10 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ለማወቅ ተችሏል፣፣



በምንጮቻችን መረጃ መስረት ለዚሁ ተግባር የፈፀሙ ሰዎች በይፋ የሚታወቁ ባይሆኑም እንኳን ከዚህ በፊት ተቃዋሚ የነበሩና በሃገሪቱ ባለው መንግስት ጥያቄአችሁንና ፍላጎታችሁን እንመልስላችሁአለን ተብለው ከገቡ በኋላ ጥያቄአቸው ያልተመለሰላቸው ሰዎች ያደረጉት ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ በአካባቢው ነገሶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣፣
  ይህ በእንዲህ እንዳለ የአካባቢው የአስተዳዳሪዎችና የፀጥታ አካላት እርስ በራሳቸው ሓይል የተሞላበት ንትርክና ያለመስማማት በመካከላቸው ተፈጥሮ ስለሚገኝ ጉዳዩ በነዚህ አካላት የተፈፀመ ተግባር ሊሆን እንደሚችልም ተጨማሪ ጥርጣሪዎች በአካባቢው በሰፊው እየተነገሩ እንደሚገኙ ከቦታው ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለመረዳት ተችሏል፣፣