Sunday, August 3, 2014

በሚኒስተር ማዓርግ የጠቅላይ ሚንስተር አማካሪ የሆነው አቶ በረከት ስምኦን ታምሞ በሳውዲ አረብ እየታከመ ባለበት ግዜ በፁኑ ክትትልና ጥበቃ ላይ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት ከወያኔ ኢህአደግ ስርዓት የበላይ ባለስልጣን አንዱ የሆነው በረከት ስምኦን ከረጅም ግዜ ጀምሮ በከባድ በሸታ እየተሰቃየ እንደቆየና  ቀደም ብሎም ወደ በደቡብ አፍሪካ በመሄድ ሲታከም ቆይቶ ሊድን ስላልቻለ፣ በአሁኑ ግዜ በፅኑ ታምሞ በሳውዲ አረቢያ እየታከመ እንደሚገኝና  ህዝብ ሁኔታውን እንዳያውቅ በማለት ስርዓቱ ልክ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ በድብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፣፣
    መረጃው አክሎ አቶ በረከት ስምኦን ገዢውን የኢህአደግ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ  እስከ አሁን ድረስ ለ23 አመታት ያክል  በከፍተኛ ሃላፊነት ተቀምጦ እየሰራ በነበረበት ሰዓት ከልክ በላይ የህዝብንና የሃገርን ሃብት ለግሉ እንዳካበትና በዚህ አስነዋሪ ስራ ላይ ከተዘፈቁት የመንግስት የበላይ ባለስልጣናት መካከል አንዱ ስለሆነ  ይህ የክትትሉና የቁጥጥሩ ሁኔታም ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመደበቅ  ሲባል እየተካሄደ ያለ ጉዳይ ነው ሲሉ ለሁኔታው ቅርበት ያላቸው ወገኖች እየተናጋገሩበት መሆናቸውን ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ትችሏል፣፣