በአማራ ክልል ከተለያዩ
ዞኖችና ወረዳዎች ለክረምታዊ ትምህርት የሚላኩ የመንግስት ሰራተኞች ከአሁን በፊት ለ3 አመት ክረምታዊና በአንድ አመት መደበኛ ትምህርታቸው
ተከታትለው ሲመረቁ መቆየታችውን በመግለፅ አሁን ግን አስራሩ በመቀየሩ ምክንያት በወረታ እርሻ ማሰልጠኛው ኮለጅ ውስጥ ያሉት ክረምታዊ
ተማሪዎች ተቃውሞ እንዳካሄዱ መረጃው አስረድቷል።
በመረጃው መሰረት የኮለጁ ባለስልጣናት በዘንድሮ አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን
የሚጠቃለልበትና የ2007ዓ/ም ሃገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት ስለሆነ ይህ ቀደም ብሎ ለክረምታዊ ተማሪዎች ሲሰራበት የቆየውን አሰራር
አስቀርተው በስድስት አመት ክረምታዊ ትምህርት ተካክሶ ከተማራቹህ በኋላ ነው የምትመረቁት ስለተባሉ ተማሪዎቹ በዚህ ተቆጥተው ተቃውሞ
በማስነሳታቸው ምክንያት ከሚሰሩበት መስርያ-ቤቶች እንደሚባረሩ ስለተነገራቸው ፈርተው ወደ ኮለጁ እንደተመለሱ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።