Tuesday, September 9, 2014

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ ኢንቨስተሮች በኢህአዴግ ታጣቂ ሓይሎች እየተገደዱ የሚሊሻዎችን መሬት በነፃ እንዲያርሱላቸው በመደረጋቸው የተነሳ ለኪሳራ ተዳረግን እያሉ አቤቱታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአሶሳና በመተከል ዞኖች ተሰማርተው የሚገኙ ባለሃብት ኢንበስተሮች የግል ስራቸውን ትተው በኢህአዴግ ታጣቂ ሓይሎች እየተገደዱ የበርካታ ሚሊሻና የገዥው መደብ ካድሬ ለሆኑ ሰዎች የእርሻ መሬት በነፃ በትራክተር እያረሱ መሆናቸውን በመግለጽ። አንዳንድ ኢንቨስትሮች ግን እኛ የግል ስራችንን ትተን በአስገዳጅ ስራ ተሰማርተን ትርፍ ማግኘት አልቻልንም በማለት መመሪያውን የተቃወሙ ኢንቨስተሮች ንብረታቸው በስርዓቱ ታጣቂዎች በመዘረፍ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው ጨምሮ እንደሚያስረዳው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስተዳዳሪዎች በአካባቢው ለተሰማሩ ኢንቨስተሮች ሰብስበው በዚህ አካባቢ ተሰማርተው የሚገኙ የመንግስት ታጣቂዎች የናንተን ንብረት ለመጠበቅ የተሰማሩ ስለሆኑ የእርሻ መሬታቸውን ልታርሱላቸው ይገባል በማለት የክልሉ የፀጥታ ሓላፊ በተገኘበት ሊያታልሏቸው በሞከሩበት ሰዓት ኢንቨስተሮቹ በበኩላቸው ማንንም አንፈልግም ንብረታችንን ራሳችንን እንጠብቀዋለን የሚል መልስ ቢሰጡም የክልሉ ባለስልጣኖች ግን መመሪያ ስለሆነ ልታርሱላቸው ይገባል የሚል መልስ እንደሰጧቸው ታውቋል።