Tuesday, September 9, 2014

በሁሉም የሃገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ያነሱትን ጥያቄ የኢህአዴግ ገዢ መንግስት ባለስልጣኖች መመለስ ስላቃታቸው ከባድ ውጥረት መፈጠሩን ምንጮቻችን አስታወቁ።



     እነዚህ በሁሉም ያገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያለፍላጎታቸው በስርአቱ ባለስልጣኖች ተገደው ስብሰባ ላይ ተጠምደው መሰንበታቸውን የገለፀው መረጃው በተማሪዎቹ የቀረቡትን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ባለመመለሳቸው ምክንያት ውጥረት መንገሱ ተገለፀ።
     በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተነሱት ጥያቄዎች አያሌ ቢሆኑም ጥቂቶችን ለመጥቀስ-
Ø የሃይማኖት መሪዎች መሳርያ ደብቀዋል በሚል ሽፋን በፀጥታ አባላት ለምን ይደበደባሉ?
Ø በ1997 ዓ/ም በተካሄደው ምርጫ ላይ ለቅንጅት የመረጡትን አርሶአደሮች። መሬታቸው ተነጥቆ ለገዢው ድርጅት አባላት መሰጠቱ ትክክል አይደለም፤
Ø በኢህአዴግ ስርዓት መሬትን ለውጭ ኢንቨስተሮች መሸጥ። ያገራችንን ሉአላዊነት የሚጥስ ትልቅ ስህተት ነው፤
Ø የአቶ አያሌው ጎበዜ ከአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ማውርድ ከመተማ መሬት ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ተማሪዎቹ ባቀረቧቸው ጥያቄዎች በመድረክ መሪዎቹ ውስጥ መደናገጥ ፈጥሮ ተገቢ መልስ ሳይሰጡበት በማለፋቸው ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን መግለፃቸው ታውቋል። 

     በተመሳሳይ መንገድ በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ካቀረቡት ጥያቄዎች።- ህወሃት በህዝብ ስም እየነገደ ነው፤ ህወሃት ለራሱ ብጥቅም እየተከፋፈለ የመጣ ድርጅት ነውና የድርጅቱ መኖር ለትግራይ ህዝብ ምን ፋይዳ ይሰጠዋል፤ የአረና ድርጅት መፈጠሩ ህወሃት ለትግራይ ህዝብ የሰጠው ጥቅም እንደሌለ ትልቅ ማሳያ ነው፤ መምህር አብርሃ ደስታ የፈፀመው ወንጀል አልመኖሩና ተቃዋሚ በመሆኑ ብቻ መታሰሩ ተገቢነት የለውም፤ በትግራይ ክልል ያለው የትምህርት ሽፋን ዝቅተኛ ነው የሚሉና ሌሎችም የተነሱ ጥያቄዎችን ተገቢ መልስ እንዳልተሰጣቸው ምንጮቻችን ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።