በመረጃው መሰረት የወለጋና የአምቦ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች በገዢው የኢህአደግ ድርጅት ስርዓት ነሃሴ 19
/2006 ዓ/ም በአምቦ ከተማ ወደሚገኘው አደራሽ በጠሩት ስብሰባ ላይ ወደ አዳራሹ ሲገቡ በኦሮምኛ የተፃፈ መፈክር ከኪሳቸው በማስወጣት
“ ኢህአደግ ሙሰኛ፤ ፀረ ህዝብ፤ በአምቦ በፖለቲካ የታሰሩት ይፈቱ፤ 2007 ዓ/ም መጨረሻህ ናት “ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን
ይዘው እየጨፈሩ በነበሩበት ግዜ የስርአቱ ባለ-ስልጣኖች ስልክ ደውለው አግአዚ ኮማንዶ ሰራዊት በማስመጣት ተማሪዎቹን እንደበተኑዋቸው
ለማወቅ ተችሏል።
40 የሚሆኑ ተማሪዎች አነሳሶች በሚል ምክንያት
ታስረው ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰዱ መረጃው ገልፆ ከታሰሩት መካከልም ታረፈ ኩማ ፤ አብዲሳ ብሪ፤ ጎርደፋ ሑረታ፤ አዲሱ ደበላ፤
በየነ ለማ፤ ኑርሳ ጌታቸው፤ የምዩ ገመቹ፤ ወልፈታ ጀጌማ፤ በዳዳ ኩምሳ፤ ታምሩ አበራና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው በመጥቀስ እነዚህ ሳይቃወሙ ስብሰባው ላይ የተሳተፉት ተማሪዎችም የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸውና
ወደየ ዩኒቨርስቲያቸው ስም ዝርዝራቸው እንደሚላክላቸው ቃል እንደተገባላቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።