Sunday, September 7, 2014

የገዢው ህወሓት ኢህአደግ ካድሬዎች የድርጅት አባላት ሁኑ በማለት አስገድደው አዳዲስ ሰዎች እየመለመሉና ስልጠና በመስጠት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ።



   የምንጮቻችን መረጃ እንደሚያመለክተው በየወረዳው በሚገኙ የህወሓት ኢህአደግ አስተዳዳሪዎች የድርጅቱ የታችኞች አመራር አባላት እንድትሆኑ በማለት አስገድደው አዳዲስ ሰዎችን በመመልመል ለ19 ቀናት ያክል የካድሬ ትምህርት በመስጠት ሲያሰለጡኑዋቸው እንደሰነበቱ ለማወቅ ተችሏል።
የስልጠናው አጀንዳም በአራት ክፍሎች የተከፈሉ ሲሆን እነሱም
1.     የድርጅቱ ታሪክ አመጣጥ
2.     የከተማ ልማትና ተሃድሶን  በማያያዝ
3.     የታችኖቹ አመራር አባላት ሊደርሱበት የሚገባቸው
4.     ቤንች ማርክ (bench mark) ማለት ምን ማለት ነው? የሚሉ ሲሆኑ፣ አራት አስልጣኞች ተመድበው 1,227 ሰዎችን በሁለት ቦታ ከፍለው ከሃምሌ 21 /2006 ዓ/ም እስከ ነሃሴ 8 /2006 ዓ/ም እንደቆዩና ስልጠናውም ገና እንደሚቀጥል መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።