Sunday, September 7, 2014

በደቡብ ክልል፤ ከፋ ዞን፤ ጫና ወረዳ፤ ባላ-ሻሻ ቀበሌ ውስጥ የሚነሩ ወጣቶች ያካባቢው መስተዳደር ወደ ቤንች-ማጂ እንዲቀይርላቸው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያትበመከለከያ ሰራዊትና በፖሊስ መደብደባቸውን ምንጮቻችን ካካባቢው ገለፁ።



    በደረሰን መረጃ መሰረት የቀበሌው ነዋሪ ህዝብ ያስተዳደር አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጫና ወረዳ  ለመሄድ ስለ-ራቀባቸውና ወደ ቤንቺ ማጂ እንዲቀየሩ በማለት  ለደህዴን-ኢህአዴግ በሰላማዊ መንገድ ስለጠየቁ ብቻ በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት የተደበደቡ ሲሆን በዚሁ ዘግናኝ ጭፍጨፋ 3 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 3 እንደቆሰሉና  25 ንፁሃን ሰዎችም ከመኖሪያ ቤታቸው ትወስደው እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል።
    የከፋ ዞን ጫና ወረዳ የባላ-ሻሻ ነዋሪዎች መፍትሄ እንዲያገኙ በማለት ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ በሰራዊቱ የደረሰባቸውን ጭፍጨፋ ዛሬም ይሁን ነገ አጥብቀን እናወግዘው አለን እንዳሉና እነዚህ የመብት ጥያቄ ስላነሱ ብቻ በስርዓቱ ከታሰሩት መካከልም አቶ ገዛኸኝ ታረቀኝ የሚባሉ ግለሰብ እንደሚገኙበት መረጃው አክሎ አስታውቋል።