የህወሃት-ኢህአዴግ ስርአት፤ ስልጣን ከወጣበት ማግስት ጀምሮ ካለፈው መራራ ትግል ባጋጣሚ በሂወት የተረፉትና አካላቸው ጎድሎው አሁን
ወዳለው መድረክ ለደረሱ ጀግኖች ለበርካታ ታጋዮች የታሪክ አተላ የሚል ስም ለጥፎ ሲያባርራቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ የህዝብ ልጆችም
በዴሞብላይዘሽን ስም ያለምንም ማቋቆምያ በየበረሃውተጥለው እንዲቀሩ ፈርዱባቸዋል።
በዚህ አስነዋሪ የስርአቱ ድርጊት በትግሉ ወቅት ሙሉ እድሚያቸውን ለትግል
ላስረክቡና ምንም አይነት የሞያ ችሎታ ያልነበራቸውን ጀግኖች ያለምንም ማቋቋሚያ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውና
በተለይም በሴት ታጋይ እህቶቻችን ላይ የደረሰው አስከፊው ጠባሳ እስከ አሁን ድረስ በህብረተሰቡ ውስጥ ያስከተለው ማህበራዊ ቀውስ
ይህ ነው የሚባል አይደለም።
ይህ ካለፈው ድርጊቱ ያልተማረው ከዳተኛ ስርአት አሁንም ፀረ ህዝብ ተግባሩን
በመድገም በወታደሮቹ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል፣ የወያኔ ኢህአዴግ ሰራዊት በስርአቱ ላይ የነበረውን
እምነት ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ በመሄዱ ምክንያት ከየ ክፍሉ እየፈረጠጠ መሆኑንና 7 አመት ያገልግሎት ጊዜያችን ስላበቃ እሰናብቱን
የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች በመስፋፋቱ ምክንያት ለመሪዎቹ ጭንቀት ላይ እንደጣላቸው ይታወቃል።
በዚህ መሰረትም ከረጅም ግዜ ተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ የጦሩ ውስጣዊ ስሜት
ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ መሪዎች ከሁሉም እዞች በርካታ ወታደሮችን እንዲያሰናበቱ መገደዳቸውና
በሽዎች የሚቆጠሩ መኮንኖችና የሰራዊቱ አባላትም አነሳሾች እየተባሉ አገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ወታደራዊ እስርቤቶች ታጉረው እየተሰቃዩ
ይገኛሉ። ይህ ድርጊትም በሰራዊቱ ውስጥ ያለው ውጥረት ይበልጡን እንዲባብስ አድርጎታል።
ስርአቱ ከዚህ በፊት የፈፀመውን አስነዋሪ ድርጊት በመድገም በአሁኑ ግዜ
እያሰናበታቸው ያለው ወታደሮች ምንም አይነት ክብር በሌለበትና የሚረባ የገንዘብ ድጋፍ ሳይሰጡ እያባረራቸው እንደሆነ፤ በቦርድ ምክንያት
ተሰናብተው ወደ ትውልድ ቦታቸው ከተሸኙ በኋላም በቦርድ መውጣታችሁን የሚገልፅ ወረቀት ሳትይዙ ስለ-መጣችሁ የምናውቀው ነገር የለም
ተብለው እየተንገላቱ እንደሆኑና የወታደር ስራ አያስፈልገንም ብለው የተቃወሙ ናቸው የሚል መሸኛ ወረቀት ተፅፎ ስለ ተሰጣቸው ባገራቸው
ውስጥ ተንቀሳቅሰውና ሰርተው እንዳይኖሩ እንቅፋት ሆነባቿል።
ላንድዶቹ የተሰጠው በጣም ጥቂትና የማይረባ ገንዘብም ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር በምንም ሊያንቀሳቅሳቸው ስላልቻለ ደማችንን
ያፈሰስንበት ስርአት ህዝባዊ ሃላፊነቱን ረስቶና ብልሹ በሆነ የጥፋት መንገድ እየተጓዘ እያየን አንገታችንን አቀርቅረን አናልፍም
በማለት ስብሰባ በሚደረግበት አጋጣሚ ላይ የመሰላቸውን ሃሳብ በማቅረብ በአስተዳዳሪዎች ላይ ሂስ በሚሰነዝሩበት ግዜ። ለሁለተኛ ግዜ
እንደዚህ አይነት ሃሳብ እንዳያቀርቡ የማስፈራርያ ዛቻ እንደሚሰነዘርላቸውና ከህብረተሰቡ እንዲነጠሉ ለማድረግም በመከላከያ ሰራዊት
በነበሩበት ግዜ ለመሪዎቻቸው የማይታዘዙ ወመኔዎች እንደነበሩ ተደርጎ በመግለፅ በላያቸው ላይ የጥላቻ ወረራ እንዲደረግና ህዝቡ የተሳሳተ
አመለካከት እንዲይዝ እየተደረገ ነው።
ስርአቱ ለሰራዊቱ እንደጓንት ተጠቅሞ እንደሚወረውራቸው ጠንቅቀው የሚያውቁት
አንዳንድ የሰራዊቱ አባላት በተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን ስላልተመለሰላቸው በግልና በተደራጀ መልኩ ስርአቱን በመተው የትጥቅ ትግል ወደ ሚያካሂዱ ድርጅቶችና ወደ ስደት እያመሩ መሆናቸውን ይታወቃል።
የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት እነዚህ በሺዎች የሚቆጠሩ የተሰናበቱና ሸሽተው
የተበትኑትን ወታደሮች ለመተካት በመላው አገሪቱ በየወረዳዎቹ ወጣቶችን ለማስታጠቅ በከፍተኛ ቅስቀሳ እንደሚገኝና በዚህም መስረት
ከ 8ኛ-10ኛ ክፍል የደረሱትን
ከእድሜ በታች የሆኑ ልጆች ሳይቀሩ ባስገዳጅነትና በጥቅማጥቅም እያታለሉ ትምህርታቸውን እያቛረጡ ወደ ውትድርና ስራ እንዲገቡ እየገፋፍውቸው
ነው።
ቢሆንም ግን ይህ ወደ ወረዳዎች እየዞሩ እያደረጉት ያሉትን አዳዲስ ሰልጣኞችን
የመመልመል ሂደት አብዛኛው ወጣት ወደ ማሰልጠኛ ከሄደ በኋላ ጠፍቶ ወደ አገሩ ስለ-ሚመለስ አጥጋቢ ውጤት ማምጣት አልተቻለም።
የስራአቱ አመራሮችና የፌደራል ፖሊሶችም ከዚህ በፊት በሰላማዊ ህዝብ
እይተወሰደ የቆየውን እርምጃ ትክክል አይደለም፤ መንግስት በፌደራል ፖሊስ እንዲፈፀም በማለት ሲያወርደው የቆየውን መመርያ እስካሁን
ለተፈፃሚነቱ ብንቀሳቀስም መሰረታዊ ስህተት እንደነበረው ግን መታወቅ አለበት ይህ ድርጊትም ከህዝቡ አይን የተሰወረ ስላልሆነ ነገ እኛን ከተጠያቂነት የሚያድነን ስላልሆነ መንግስት በዚህ
ጉዳይ እየተከተለው ያለውን መንገድ ማስተካከል አለበት ሲሉ ተቃውሞ ማቅረባቸውንና ለወደፊቱም ወደ እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ተግባር
እንደማይገቡ የገለፁበት ሁኔታ እንደነበር ይታወቃል።