Sunday, September 7, 2014

የህወሃት ኢህአዴግ ስርኣት ቀደም ሲል በማይጨው ከተማ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ይሰራል በማለት መሰረተ ድንጋይ ቢያስቀምጥም በአሁኑ ሰዓት ቃሉን በማጠፉና ትተነዋል በማለቱ ምክንያት ያካባቢው ነዋሪ ህዝብ ይህንን ተግባር ስለተቃወመ ብቻ ያልምንም ወንጀል ወደ እስር ቤት እያጎሩት መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



     በምንጮቻችን መሰረት በትግራይ ደቡባዊ ዞን፤ በማይጨው ከተማ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች ለማስመሰል ከጥቂት አመታት በፊት በአካባቢው ተንቀሳቅሰው በነበሩበት ግዜ ለከተማው ህዝብ በመሰብሰብ ቀጣይ አመት ደረጃውን የጠበቀ ዩኒበርሲቲ ይሰራላችኋል ብለው የመሰረተ ድንጋይ ቢያስቀምጡም ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ትተነዋል በማለታቸው ያካባቢው ህዝብ ነሃሴ 18/2006 ዓ/ም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሞን ማሰማቱ ብቻ  የስርአቱ የጸጥታ ሃይሎች  አነሳሾች ናችሁ በሚል ምክንያት 9 ሰዎችን አስረው እያሰቃይዋቸው መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታው ተገለፁ።
    የከተማውና ያካባቢው ማህበረሰብ በተገባው ቃል መሰረት ልጆቻችን በቅርብ ርቀት እናስተምራቸዋለን እያልን በጉጉት እየጠበቅን ብንቆይም የድርጅቱ ባለስልጣኖች ግን ቃላቸውን በመለወጥ አሁን ለሌላ ዩኒቨርሲቲ ነው የምናጠናክረው ማለታቸው ተከትሎ ሃብቱ በርሄ የተባለው የማይጨው ቴክኒክ ኮለጅ ተማሪ የሚገኝበት 9 ተማሪዎች ሁኔታውን በመቃወማቸው ምክንያት እንደታሰሩና ያካባቢው ህዝብም ልጆቹ ካልተፈቱ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ እነደሚያካሂድ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።