Thursday, September 4, 2014

የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከክፍላቸው እየፈረሱ በመጥፋታቸው ምክንያት ስርአቱ አዲስ ወታደሮችን ለመመልመል ከፍተኛ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ተገለጸ።



    በመረጃው መሰረት የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት የህልውናው መሰረት አድርጎ የሚያስበውን የመከላከያ ሰራዊት ሃይል በየቀኑ ካለበት ክፍል እየተበታተና እየፈረሰ በመሆኑና ከባድ ስጋት ላይ ስለወደቀ ታማኝ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላት በማሰማራት አዲስ ምልምል ወታደሮች ለማስታጠቅ ቅስቀሳ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ታወቀ።
    ይሁን እንጂ ቅስቀሳ እየተካሄደባቸው ያለው ወጣቶች ለረጅም አመታት ከናንተው ጋር ላገለገሉ ወታደሮች በክብር እንዲሰናበቱ አላደረጋችሁም፤ ነገ እኛንም የነሱ እጣ ይደርስብናል ብለው ጥሪውን ስላልተቀበሉት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችና ስርአቱ ጭንቀት ላይ መግባታቸውን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።