ምንጮቻችን የለኩልን መረጃ እንደሚያመልክተው
ነሀሴ 18/2006 ዓ.ም የራያ ባህላዊ ልብስ ለብሰው በመቐለ ከተማ ሃውዜን አደባባይ አካባቢ የአሸንዳ በዓልን ሲያከብሩ በነበሩ
ወጣቶች ፖሊሶቹ በመካከላቸው ገብተው ሊበትኗቸው በሞከሩበት ጊዜ በመካከላቸው ግጭት እንደተፈጥረና በግጭቱ ምክንያትም አንድ ፖሊስ
በከባድ ሲቆስል በተመሳሳይ ሌላ ፖሊስም ተመጣጣኝ ጉዳት እንደደረሰበት የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
ለተፈጥረው ግጭት እንዲያግዙ ተብለው የመጡ
ፈጥኖ ደራሽ በመባል የሚታወቁ ታጣቂዎች የአሸንዳ በዓልን እያከበሩ ለነበሩ ወጣቶች በሁለት ፓትሮል ጭነው አድራሽው ወደ አልታወቀ
ቦታ እንደወሰዷቸው ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል።