ነዋሪዎቹ በገዢው መንግስ
እየወረደባቸው ያለውን ግፍና ማህበራዊ ችግር መፍትሄ እንዲደረግለት በማለት ነሃሴ 14/ 2006 ዓ/ም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ
በበሞከሩበት ሰአት በተቃውሞው ስጋት ላይ የወደቁ የከተማዋ ባለ ስልጣኖች የፌደራል ፖሊስና አግአዚ ኮማንዶ በማሰማራት ተቃውሞ ላይ
ለተሳተፉት ነዋሪዎች በዱላ እየደበደቡ እንደበተኗቸው ለማወቅ ተችሏል።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ላይ ህዝብ መንግስትን መቃወምና
የመሰለውን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ መብቱ እንደሆነ ግልፅ በሆነ መንገድ የተቀመጠ ቢሆንም የስርአቱ ባለ ስልጣኖች ግን ህገ መንግስቱን
ለነሱ በሚመች መንገድ እየቃኙ ከወረቀት በማያልፍ መንገድ ትርጉም እያሳጡት መሆናቸውን ምንጮቻችን ህዝቡን መሰረት በማድረግ የላኩልን
መረጃ አስታውቀ።