Friday, January 9, 2015

በአማራና በትግራይ ክልል ነዋሪዎች መካከል ግጨው በተባለው አካባቢ ላይ መሬት መነሻ ያደረገው ግጭት መፍትሄ ስላልተደረገለት በከፋ መልኩ እየቀጠለ መሆኑን ተገለፀ።



ከአካባቢው የተገኘው መረጃ እንዳስረዳው የአማራና የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሆኑ ወገኖቻችን፣ ግጨው በተባለው አካባቢ መሬት መነሻ ያደረገ ግጭት ላይ መቛጫ ስላልተደረገለት አሁንም እየቀጠለ መሆኑንና በውጤቱም ታህሳስ 19 / 2007ዓ/ም በተካሄደው ግጭት ቁጥራቸው ብውል ያልታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲሞቱ 2 ደግሞ በከባድ ሁኔታ ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተውስደው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።
   መረጃው አክሎም ግጭቱን ለማረጋጋት ተብለው በርካታ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ቦታው ቢሄዱም በአንጻሩ ግጭቱን እያባባሱት እንዳሉና ገዥው ስርአት የቡዙ ሰው ህይወትን እያጠፋና የአካል ጉዳት እያደረሰ ባለበት በአሁኑ ሰአት መፍትሄ ሊያበጅለት ባለመቻሉ ምክንያት ነዋሪዎች በስርአቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።