በስራው እንዳይሰማሩ የተከለከሉት እነዚህ የድሮ ታጋዮች እንዳሉት ለአገራችን እና ለህዝባችን ብለን አካላችንን የጎደለንና የተጎሳቆልን ሰዎች
ሰርተን ንሮአችንን እንግፋ በማለታችን ብቻ አስተዳደሩ እንደጠላት ቆጥሮ እንዳንሰራ በማገድ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብቻ ነው የሚሰሩት
ብሎ መወሰኑ የሚያሳዝን ተግባር ነው ማለታቸውን የደረሰን መራጃ አስታወቀ።
ይህ በንዲህ እንዳለ በአብይ ዓዲ ከታማ ያለው የመጠጥ ውሃ እጥረት አመታት
ያስቆጠረ ቢሆንም የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው መፍትሄ ባለማድረጋቸው ምክንያት የከተማው ነዋሪ ህዝብ ውሃን ለመፈለግ ረጅም
ቦታ ተጉዞ የሚያመጣው ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ህፃናቶች በውሃ ወለድ በሽታዎች እየተሰቃዩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።