Monday, September 22, 2014

የአብይ አዲ እስተዳዳሪዎች በማህበር ተደራጅተው በመስራታቸው ብቻ በአይን ጥርጣሬ ሲመለከትዋቸው የነበሩትን ከ 50 በላይ የቀድሞ ታጋዮች ሲሰሩበት የቆዩትን ቦታ እንደነጠቃቸው ተገለፀ።



    ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት ከዚህ በፊት ለተደረገው ትግል ከድርጅቱ ጋር  ተሰልፈው ድርሻቸውን ለተወጡ የቀድሞ ታጋዮች ከዳተኞቹ የህወሃት አመራር ስልጣን ላይ ከተቆጣጠሩ በኋላ የተባረሩ ታጋዮች በትግራይ ማእከላዊ ዞን በአብይ ዓዲ ከተማ በማህበር ተደራጅተው በመስራታቸው ብቻ ስርአቱ ስጋት ላይ ስለወደቀ በህጋዊ መንገድ ከተሰጣቸውን መሬት እንዲለቁ ማድረጉን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
     በህጋዊ መንገድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩበት የቆዩትን ቦታ በከተማው በሚገኝ 2 ደረጃ ት/ቤት አካባቢ ስለሆነ ተማሪዎቹን እያገኙ ፀረ ኢህአዴግ መንግስት እንዳያነሳሱ በማለት በስራቸው መሃል እየገባ እያደናቀፋቸው መቆየቱንና ለዚሁ አደናቃፊ ተግባር በመቃወም ባስተዳደሩ ላይ ክስ ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እናዳላገኙ የገለጸው መረጃው በአንፃሩ የአካባቢው አስተዳደር ግን ለቀድሞ ታጋዮቹ ያልሆነውን ምክንያት በመደርደር ከተሰጣቸው ቦታ ያለምንም ተለዋጭ መሬት እንዲለቁ ማድረጉን ተገለጸ።
     እነዚህ በህወሃት የትግል ወቅት አካላቸው የጎደሉት ዜጎች ተደራጅተው በመስራት ንሮአቸውን እንዳይመሩ ፊልሞን የተባለ የወረዳው እስተዳዳሪ ስልጣኑን ተጠቅሞ ሲያደናቅፋቸውና ሲበድላቸው በመቆየቱ ምክንያት ስሜት ውስጥ የገቡት እኒህ ማህበርተኞች ባላዩ ላይ የመበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ በሚል ሰበብ ወደ መቀሌ ከተማ እንዲቀይሩት ቢያስቡም የከተማው ህዝብ ግን ይህ ግለሰብ በደል ስለፈፀመ እንፋረደዋለን እያለ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረቷዋል።