Tuesday, September 9, 2014

በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የሚማሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በርከት ያሉ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ምክንያት የኢህአዴግ ገዥው መደብ በከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከአካባቢው በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



ተማኝ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለከተው በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ማለት፤ በአምቦ፤ በጅማ፤ በአዳማ፤ በሃራማያና፤ በወለጋ፤ ተማሪዎች ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም የተወሰኑትን ለመጥቀስ- 
  • በፍልሰታ ፆም ስጋ እንድንበላ ማስገደዳችሁ ሃይማኖትን ማራከስ ነው?
  • በክልላችን በተማሪዎች መካከል የሚነሱ የተለያዩ ግጭቶች መነሻቸው ገዥው ስርአት ነው?
  • በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የተነሳ ለተገድሉ የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ተጠያቂው ኢህአዴግ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል! በማለት ተማሪዎቹ መናገራቸው ሊታወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይ በደቡብ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከልም-
·         ታስረው የሚገኙት የወላይታ ሰዶ የሃገር ሽማግሌዎች ለእስር የሚዳርግ ህጋዊ ማስረጃ የለውም!
·         በሃገራችን የትምህርት ጥራት ጠቅልሎ የለም የሚሉና ሌሎችም በተማሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች እንደነበሩ የገለፀው መረጃው በተለይ  ከሃገራችን መሬት ዜጎቻችንን በማፈናቀል ለምን ለኢንቨስተሮች ተሰጠ በማለት ሙሉጌታ በተባለው ተማሪ የተገለፀው ሃሳብ ለበረካታ ተማሪዎች ህሊናቸውን እንደነካቸው ለማወቅ ትችሏል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ስለ-ፍትህ፤ የጋዜጠኞች መታሰር፤ በተለይ በደሴ ከተማ የተገደሉ ኢማም ሸኽ ኑር በገዥው መደብ የተገደሉ መሆናቸውንና ሌሎችም የሃገራችንን ነባራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን የሚፈትሹ በርከት ያሉ ጥያቄዎች በማንሳታቸው ምክንያት የስርዓቱ ባለስልጣናት በጭንቀትና በፍርሃት ውስጥ መግባታቸውን የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድተዋል።