በምንጮቻችን
መረጃ መስረት በስርዓቱ ተገደው ስለጠና ላይ የሰነበቱ የሃገራችን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተሰጣቸው ላለው ስልጠና እየተቃወሙት
እንደሚገኙ በመግለፅ ይህ የስርዓቱ ተንኮል በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄደ ያለ ሲሆን በተለይ
በመቐለ ከተማ የሚገኙ ሰልጣኞች በስልጠናው መክፈቻ እለት ስለ-ስልጠናው አላማ የሚመለከት በሰማታት አዳራሽ ውስጥ በሚነገሩበት
ሰዓት ሰዓቱ የእረፍት ጊዜአችን ስለሆነ ያለምንም አበል አንሰልጥንም በማለት የእምቢታ መልስ አሰምተው እንደነበረ ለማወቅ
ተችሏል።
የህወሃት ኢህአዴግ ገዠው ድርጅት ግን በተላላኪ የፀጥታ አስከባሪዎችና
ካድሬዎቹ በኩል አድርጎ ለእረፊት የመጡትን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአስገዳች ወደ ስልጠናው እንዲገቡ ማድረጉንና የተወሰኑ
ተማሪዎች ግን እስካሁን ስልጠናውን አንካፈልም በማለት ተቃውሞአቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ በመግለፅ ስልጠናውንም እየመራ የሚገኘው
የቀድሞው ታጋይ መኮነን አስፋው የተባለው የመቐለ ዞን “እቶት” ሓላፊ መሆኑን የገለፀው መረጃው ይህ የስርዓቱ ካድሬ ለስልጠና
ብሎ ይዟቸው ከቀረበው ነጥቦች የተወሰኑትን ለመጥቀስ የህወሃት ድርጅት ከ1968 ዓ,ም ጀምሮ እስካሁን እንዴት ብሎ እንደመጣ
የሚያሳይ በተለያዩ ፊልሞችና ፅሁፎች እያቀናጀ ሰሚ አካል
በሌለበት ብቻውን ሲባዝን እንደሰነበተ ሊታወቅ ተችሏል።
በነበረው መድረክ ላይ በተማሪዎች ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል
የተወሰኑት ለመዘርዘር ያክል-