Sunday, September 14, 2014

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የፋይናንስ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች ለነጋዴዎች ግብር እንቀንስላችሁአለን በማለት ጉቦ እየበሉ እንዳሉ ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ።



     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ በፋይናንስ ፅህፈት ቤት ተመድበው እየሰሩ ካሉት ንጉሴ ዋኘው የተባለ ግለሰብ ነጋዴዎችን ግብር በማስከፈል እቀንስላችሁ አለሁ እያለ ከ20 ሺህ ብር በላይ ጉቦ እንደተቀበለ ተገለጸ።
   ነጋዴዎቹ ጎቦ ሳንከፍል የንግድ ስራችንን ልናሳልጥ አንችልም በማለት በጉቦ ስራ ተሰማርቶ ያለው የምንግስት ስራተኛ በሚከሱበት ግዜ ስርአቱ ምንም አይነት እርምጃ ስላልወሰደበት ነጋዴዎችና ያከባቢው ነዋሪው ህዝብ ብሶታቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ ካገኘነው መረጃ ለማወቕ ተችሏል።
   መረጃው ጨምሮ የኢህአደግ ከፍተኛ ባለ-ስልጣናት በሙስና የተዘፈቁ ስለሆኑ የበታችኞቹን ሰራተኞች ትክክለኛና ህዝባዊ አገልግሎት እንደማይሰጡ እንዲሁም ጎቦኞች መሆናቸውን አስገንዝቧል።