Sunday, September 14, 2014

በዳሉል ወረዳ የሚገኙ የሰሜን እዝ ሰራዊት የመንገድ ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ነሃሴ 24 2006 ዓ/ም ባካሄዱት ተሃድሶ ለመለስ ፋውንዴሽን መስርያ እንዲያዋጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉት ታወቀ።



    ምንጮቻችን ከአከባቢው እንዳስረዱት በአፋር ክልል ዳሉል ወረዳ ልዩ ስሙ ሓመድ ዒላ በተባለው ቦታ የሚገኙ የሰሜን እዝ የመንገድ ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ነሃሴ 24 2006 ዓ/ም ብዙ ወጪ ተደረጎለት የተካሄደው ትልቅ ተሃድሶ የክብር እንግዳ ሆኖ የተገኘው በመከላከያ ሰራዊት ምኒስቴር ዲኤታ ብርሃነ ነጋሽ ለመለስ ፋውንዴሽን እንድንሰራ ለሱ የሚሆን ገንዘብ እናውጣ ሲል ያቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት እዳላገኘ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
    ባለ ስልጣኑ በተሃድሶው ለመገኘት ያስገደደው ዋናው ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የሰሜን እዝ ሰራዊት የመንገድ ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ሁሉ ግዜ በመጠጥ ምክንያት ከሴቶች ጋር ስለሚጣሉና ይህንን ለማረጋጋትና በመለስ ዜናዊ ስም ገንዘብ አዋጥተው ማስታወሻ ለምስራት በሚል ሃሳብ ማንሳት ሲጀምር እነዚህ ለመዝናናት የመጡት የሰራዊቱ አባላት ልንዝናና ነው የመጣነው እንጂ ገንዘብ ልናዋጣ አልመጣንም በማለት ሃሳቡን እንደተቃወሙት መረጃው አስረድቷል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን እዝ ለሚገኙ የአምሳ አለቃ ማአርግ ያላቸው የስራዊቱ አባላት ወደ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማእከል እዲገቡ ነሃሴ 27 2006 ዓ/ም በተሰጣቸው የመለያ ፈተና አድልዎ የተሞላው እንደነበረ ተጎጂዎችን መሰረት በማድረግ መረጃው አስረድቷል።
  በደረሰን መረጃ መሰረት እነዚህ ወደ ማስለጠኛው የለፉት ሰዎች መለያ ተብሎ ለአምሳ አለቃ መአርጋቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተሰጠ ፈተና ለይስሙላ እንጂ ያለፉትንና የወደቁትን አስቀድሞ የተጨረሰ በሞሆኑ በፈተናው ጥሩ ውጤት ያመጡ የተለያዩ ተንኮሎችን ተጠቅመው እንዲቀሩ ስላድረጓቸው እነዚህ ተበዳዮች የገዢውን ድርጅት አስራር በምሬት እየነቀፉት እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።