Sunday, September 28, 2014

የግል ስራቸውን ለማከናወን ወደ መረብ ወንዝ አካባቢ የተንቀሳቀሱ ወጣቶችን ከተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛላችሁ በሚል ሰንካላ ምክንያት እየታሰሩ መሆናቸው ተገለፀ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ መደባይ ዛና ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ስራቸውን ለማከናወን ወደ መረብ ወንዝ አካባቢ እንዳይሄዱ እንደተከለከሉ የገለፀው 19 የወረዳው ወጣት  ነዋሪዎች መስከረም 1/2007 ዓ/ም ዘንበባ ለማምጣት ወደ መረብ ወንዝ በመሄዳቸው ወደ አካባቢው የሄዳችሁበት ምክንያት የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች ጋር ልትገናኙ ስለፈለጋችሁ ነው በሚል ተጨባጭነት የሌለው ሰለክለካ ከተማ ውስጥ ወስደው እንዳሰሯቸው ለማወቅ ተችሏል።
    ከታሰሩት ወጣቶች የተወሰኑትን ለመግለፅ።-
-    ኤፍሬም ቀጭኑ
-    ምስግና መዓሾ
-    ሓሰን ዑስማና ቴድሮስ አማረ የተባሉ እንደሚገኙባቸው የጠቀሰው መረጃው የንፁሃኑ ታሳሪ ቤተሰቦችም ልጆቻቸውን እንዳይጠይቁ በተለየ ሁኔታ ይዟቸው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።