Tuesday, September 16, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ ገዥው መደብ ተላላኪ የሆኑ ካድሬዎች እያወረዱት ባለው በደል ክፉኛ የተማረረው የጎንደር ከተማ ህዝብ በላያቸው ‘ላይ የመግደል እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገለፁ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ጎንደር ‘ከተማ የሚገኙ የስርዓቱ ወሮ-በላ ካድሬዎች ህዝብ የሰጣቸውን አደራ ወደጎን በመተው በሙስናና የሰውን መብት በመጣስ ስራ ላይ መሰማራታቸውን የታዘበው የጎንደር ከተማ ነዋሪ ህዝብ በላያቸው ላይ የመግደል እርምጃ እየወሰደ እንዳለ በመግለጽ የግድያ እርምጃ ከተወሰደባቸው የስርዓቱ ተላላኪዎች አንዱ አላምረው ደጀኔ የተባለ የቀበሌ 06 አስተዳደር የነበረ ሲሆን ይህ በነሃሴ 24/2006/ዓ,ም በመጠጥ ቤት እያለ በአቶ መኮነን ስልጣን በተባለ የከተማዋ ነዋሪ ተገድሎ እንደተገኘ ምንጮቻችን ‘ከአካባቢው አስታውቀዋል።
  በነዚህ ፋሽስት የኢህአዴግ ካድሬዎች ላይ ህዝቡ እየወሰደው ያለው የመግደል እርምጃ በጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች በሰፊው እየተከናውነ ያለ ጉዳይ ነው ሲሉ ምንጮቻችን አክለው አስታውቋል።