Tuesday, September 16, 2014

የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች እያጋጠመማቸው ላለው የኤሌክትሪክና የኔት ወርክ ችግር መፍትሄ እንዲደረግላቸው በማለት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸውን ስላቀረቡ የስርዓቱ ካድሬዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ፈጥራችኋል በሚል ምክንያት ለህብረተሰቡ ስብሰባ ላይ ጠምደውት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።



  በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በሚገኙ ከተማዎች እያጋጠመ ባለው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ሓይልና ኔት-ወርክ መቆራረጥ ምክንያት ህብረተሰቡ ዕለታዊ ኑሮውን መምራት ስላልቻለ ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታቸውን ስላቀረቡ ብቻ የተበሳጩ የስርዓቱ ባለስልጣናት በውስጣችን አሸባሪዎችና የአሸባሪ ተላላኪዎች  ተሰራጭተዋል  በማለት ስጋት ውስጥ ስለገቡ ለነዚህ ውስጣችን ገብተው ላሉት አሸባሪዎች ለማጋለጥ  ህብረተሰቡ የበኩሉን ማድረግ አለበት በማለት ቀጣይነት ባለው ስብሰባ ጠምደውት እንደሚገኙ ምንጮቻች ገለፁ።
    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የከተማዎቹ ነዋሪዎች ከምንም ጊዜ በላይ ምሬታቸውን ከፍ አድርገው በመግለፃቸው ድንጋጤ ውስጥ የገቡ የስርዓቱ ካድሬዎች የህዝቡን ከፍተኛ አቤቱታ አቅጣጫውን ለመቀየር ነሓሴ 19እና 20 2006 ዓ.ም ለህብረተሰቡ ስብሰባ በመጥራት እየቀረበ ያለው አቤቱታ ትክክለኛ ያልሆነና በአሸባሪዎች የተቀነባበረ ስለሆነ ይህ ደግሞ ከማንም የተሰወረ ባለመሆኑ ለነዚህ አሸባሪዎች ህዝቡ እራሱ ማጋለጥ አለበት በማለት ለማስፈራራት የሞከሩ ቢሆንም ህዝቡ ግን ምንም አይነት የፍራቻ ምልክት ሳያሳይ አቤቱታውን በማሰማት ‘ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
    በተለይ ደግሞ በፉነተ-ሰላምና በቡሬ ከተማ የተካሄደው ስብሰባ በወጣቶች ላይ ያተኮረ እንደነበረ በመግለጽ ህብረተሰቡ እንዲፈራና በአይን ጥላቻ እንዲተያይ ንፁሃን ዜጎቻችንን አስረው እያሰቃዩዋቸው እንዳሉ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።