Tuesday, September 16, 2014

የቃፍታ ሁመራ አስተዳዳሪዎች ነሃሴ 12/2006 ዓ/ም ላይ የባዕኸር ነዋሪዎችን በሰበሰቡበት ግዜ ህዝቡ መሬታችንን እየነጠቃችሁ ለሃብታሞች እሸጣችሁት ነው በማለት ብሶታቸውን መግለፃቸው ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



     በመረጃው መሰረት የወረዳው አስተዳዳሪዎች ከባለሃብቶች ጋር በማበር  መሬታችሁን በሚገባ አልተከታተላችሁትም በሚል ከእውነት የራቀ አሰራር በርከት ላሉ ያካባቢው ነዋሪዎች መሬታቸውን ተነጥቀው ሚኬኤለ ለተባለው ኢንቨስተር መስጠቱ ትክክል እንዳልሆነና በስብሰባው ላይ እንደ ማስረጃ ተደርጎ መነሳቱም ተገለጿል።
     መረጃው በመቀጠል ተሰብሳቢው ህዝብ እናንተ ያያዛችሁትን ስልጣን ተጠቅማችሁ የእርሻ መሬታችንን እየነጠቃችሁ በመሸጥ ልትበሉት ስለፈለጋችሁ እንጂ በቅንነት ቢሆን ህዝቡን እየተበደለ ነው የሚል ተደጋጋሚ ጥሪ እየመጣላችሁ ለምን ተለዋጭ መሬት ይሁን ካሳ እንዲሰጥ አላደረጋችሁትም? በፈፀማችሁት መጥፎ ድርጊት በርካታ ህዝብ ለችግር ተጋልጧል ብለው እንደተናገሩ ለማወቅ ተችሏል።
     ከወረዳው ሳንወጣ የህርሲ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እቶ ሃይለ ገብረዝጊአብሄርና ጣሂር ፋራህ የተባሉ የሚገኙባቸው መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም ብለው ለወረዳውና ዞን አስተዳዳሪዎች በመቃወም እስከ ፌደራል ሄደው ብሶታቸውን ቢያቀርቡም የሚሰማቸው አካል በማጣታቸው ምክንያት አንዳችም የእርሻ ስራ ማከናወን እንዳልቻሉ መረጃው አክሎ አስረድቷል።