Thursday, September 4, 2014

በደቡብ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ የጋሞጎፋ ዞን ነዋሪዎች ለወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳደረጉ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገልፁ።



    በመረጃው መሰረት ከ2500 በላይ የሆኑ የጋምጎፋ ነዋሪዎች ስርዓቱን በመቃወም ሰፊ የሆነ ሰላማዊ ሰላፍ እንዳካሄዱ በመግለፅ እነዚህ ሰልፈኞች እያሰሟቸው የነበሩ መፈከሮችም ፖለቲካዊ ደህንነታችን ይከበርልን፤ ማህበራዊ አገልግሎት እንደ ጤና፤ ትምህርትና የኑሮ ደረጃችን ይሻሻልልን የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች በሰልፈኛው ተነስተው እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህንን ሰልፍ ሲያስተባብሩና ሲመሩት የነበሩ አካላት በመጀመሪያ በስርዓቱ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን በስርዓቱ ተላላኪ ካድሬዎችና በስውር ለመጥለፍ በተሰማሩ ሓይሎች በጥብቅ እየተፈለጉ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስታውቋል።