Thursday, September 4, 2014

በዚህ ሰሞን በትግራይና በአፋር ክልል መካከል በተፈጠረ ሃይለኛ ግጭት በርካታ ሰዎች ለሞትና ለመቁሰል አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸውን ታውቋል።



    ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት የአፋር ክልል ኮነባ ወረዳ ዋሕደስ ቀበሌ የሚኖሩ ሰዎች ከትግራይ ክልል አፅቢ ወምበርታ እሶት ቀበሌ 10 ከብቶች ከእረኞች ቀምተው ስለወሰዱ ለእነዚህ ከብቶች ለማስመለስ የሄዱ ሰዎች ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ለማወቅ ተችሏል።
     በተከፈተው ተኩስ ከእሶት ቀበሌ አንድ ሰው ሞቶ ሁለት ሰዎች ሲቆስሉ ከአፋር ክልል ዋሕደስ ቀበሌ ደግሞ ሁለት ሞተው 3 ደግሞ መቁሰላቸውና በተፈጠረው ግርግር መካከልም 20 ከብቶች ከአፋር ወደ ትግራይ መወሰዳቸውን መረጃው አስረድቷል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ከበራህለ  ገማል ወረዳ፤ ከቢል ብራንና ወራየ ከተባሉት ቀበሌዎች ለማገዝ ሰዎች ወደ  ኮነባ ወረዳ ስለሄዱ  የስርዓቱ ሰራዊት ለይምሰል ችግሩ ለመፍታት በመካከላቸው ቢገባም እስካሁን ድረስ ግጭቱ ሊበርድና ሊረጋጋ እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል። 
    መረጃው በማከል ዋናው የግጭቱ መነሻ ከብቶች መወሰዳቸው ሳይሆን ስርዓቱ እየተከተለው ባለው  ፍትሃዊነት የጎደለው የመሬት አስተዳድርና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል የመሬት ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን አስረድቷል።