Tuesday, September 2, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ሽሬ እንድስላሴ ውስጥ የሚገኙ የስርአቱ አስተዳዳሪዎች የመጠጥ ባለቤት በሆኑ ባለድርጅቶች መሃል እየገቡ እርስ በርሳቸው እያጋጯቸው እንደሆኑ ከአባቢው በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የሽሬ ከተማ አስተዳዳሪዎች በበዴሌና ዳሸን ቢራ አካፋፋዮች ጣልቃ በመግባት ባልተፈለገ ውድድር ውስጥ ገብተው እንዲጣሉ በመደረጉ ምክንያት ነሃሴ 12/2006 ዓ/ም በሰው ሂወት ላይ የሞት አደጋ እንዳስከተለ ለማወቅ ተችሏል።
     በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የ04 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው አቶ ግደይ ካሕሳይ ነዋሪነቱ 03 ቀበሌ ለሆነው አቶ ደገፉ መኮነን መግደላቸውን የደረሰን መርጃ አክሎ አስረድቷል።