ይህ በጭልጋ ወረዳ፤
ልዩ ስሙ አርሴማ በተባለው አካባቢ ከሚገኘው ቤት ክርስትያንና የጠበል ውሃ በየግዜው ከመእመናን የተገኘውን ገንዘብ ስራ ላይ ሳይውል
እየተጠፋፋ እንደሆነ የገለፀው መረጃው በካድሬዎቹ ጣልቃ ገብነት ምክንያት፤ በቤተ ክርስትያኑ አገልጋዮችና ባካባቢው በሚገኝ የቅማንት
ብሄረሰብ ገንዘቡን ለመውሰድ በተከሰተው ግርግር በሂወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን መረጃው አሳታወቀ።
በተፈጠረው ግርግር ምክንያት ነሃሴ 12/2006 ዓ/ም ፍሬው መኳንንት
የተባለው አንድ የቤተ ክርስትያኑ አገልጋይ ተደብድቦ መሞቱንና ይህ ድርጊት እንዲፈጸም የቻለውም በወረዳው አስተዳዳሪዎች ቸልተኝነት
ምክንያት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።