Tuesday, September 2, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚኖር ህዝብ መሰረታዊ ሸቀጦችን በማጣቱ ምክንያት ህይወቱን ለመምራት ተችግሮ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታወቁ።



     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በሁመራና በዳንሻ አካባቢዎች የሚገኝ ህብረተሰብ  ለዕለታዊ ህይወቱ የሚያስፈልጉ እንደ ስኳር፤ ዘይትና ተዛማጅ ነገሮች ከገባያ ጨርሰው በመጥፋታቸው ምክንያት እሮሮአቸውን እያሰሙ እንድሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
   ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት የኢህአዴግ ገዥው መደብ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በማሰብ ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ አላቂ ነገሮችን በአባሎቹና በካድሬዎቹ በኩል አድርጎ ለህብረተሰቡ እንዲከፋፈል ካደረገ ወዲህ ጀምሮ በአካባቢው ከመጠን በላይ የሆነ የገባያ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደሚገኝና የዚህ ዋነኛ ምክንያትም እነዚህ ከመንግስት ለህበረተሰቡ እንዲያከፋፍሉ ተብለው የተመደቡ የስርዓቱ ዋነኛው ካድሬዎች በተገቢው መንገድ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ባለማከፋፈላቸውና በመጋዝናቸው በማሸግ ጨርሰናል  በማለት ከዋጋው በላይ ለሚገዟቸው የህብረተሰብ ክፍል ግን በሌሊት ደብቀው እየሸጡላቸው እንደሚገኙ  ታውቋል። 
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው ተፈጥሮ ባለው ‘የኤሊክትሪክ መቆራረጥና የኔት-ወርክ አለመኖር የተነሳ የአካባቢው ህብረተሰብ ዕለታዊ ህይወቱን እንዳይመራ እንቅፋት ገጥሞት እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስታውቋል።