Tuesday, September 16, 2014

ወታደሮች ጭና ከአዲ ሃገራይ ወደ ማይ ሑፃ ትጓዝ የነበረችው ኦራል መኪና በመገልበጥዋ ምክንያት ባላይዋ ላይ የነበሩ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



የ8 ሜካናይዝድ ተሽክርካሪ የሆነችው በሰሌዳ ቁጥር መከ 02607 የምትታወቀው ኦራል ወታደራዊ መኪና ነሃሴ 25/2006 ዓ/ም ስብሰባ ላይ የቆዩትን መኮንኖች ጭና ከአዲ ሃገራይ ማይ ሑፃ ወደተባለው ቦታ እየተጓዘች በነበረችበት ሰአት የመገልበጥ እደጋ እንደደረባት የገለጸው መረጃው ተሳፍረው የነበሩት ወታደሮች የሞትና የመቁሰል እደጋ እንዳጋጠማቸው የተገኘው መረጃ ገለፀ።
    መረጃው ጨምሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት 15 ወታደሮች ወዲያውኑ ሲሞቱ ከ14 በላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውና የዚህ አደጋ ምክንያትም ተሽከርካሪዋ ከመጠን በላይ እንድትጭን በመደረጉ ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
    ባካባቢው በተሽከርካሪ አደጋ የሚደርሰው ጉዳት የተለመደ መሆኑንና ይህም የበላይ አመራሮቹ በሚደርሰው ጉዳት ላይ ትኩረት ስለ ማይሰጡበት ነው በሚል በሰራዊቱ ውስጥ በሰፊው እየተነገረ መሆኑን ከክፍሉ ሸልኮ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።