Tuesday, September 16, 2014

የ2006 ዓ/ም የበጀት መዝግያ ምክንያት በማድረግ አዊ ዞን በሚገኙ የወረዳ ፅህፈት ቤቶች በተካሄደው የማስመሰል ግምገማ ላይ ህጋዊ ባልሆነ መገድ ሂስ የተደረገባቸው ሰራተኞች ከስራቸው እንደተባረሩ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በአማራ ክልል፤ አዊ ዞን በሚገኙ የወረዳ ፅ/ቤቶች የ2006 ዓ/ም የበጀት መዝግያውን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ግምገማ ላይ ስልጣን ላይ ለሚገኘው የብአዴን ኢህአዴግ ገዢ መደብ ደጋፊዎች አይደሉም ተብለው የተጠረጠሩትን በርከት ያሉ ሰራተኞች በተደራጁ የስርአቱ ካድሬዎችና ግለሰቦች ሂስ ተደርገው ስራቸውን እንዲለቁ እንደተገደዱ ተገለፀ።
     ምንጮቻችን ጨምረው እንዳስረዱት እነዚህ ጥቃት እንዲደርስባቸው የተፈለጉት ሰራተኞች ከዚህ በፊት ምንም አይነት ጉድለት ቀርቦላቸው እንደማያውቅ የገለጸው መረጃው  መንግስታችን በኪራይ ሰብሳቢነት አየተወቀሰ ያለው በናንተው ብልሹ አሰራር የተነሳ ነው ተብለው ከተገመገሙ በኃላ 13 የወረዳ ኃላፊዎች ስራቸውን እንደለቀቁ ለማወቅ ተችሏል።
     ስራቸውን ከለቀቁ ግለሰቦች ከፊሎቹን ለመግለፅ-
-    አቶ አጉማስ ከአንከሻ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት
-    አቶ ደጉ አመራ በጃዊ ወረዳ የማዛጋጃ ቤት ምክትል ሃላፊ የነበረ
-    እቶ ግርማ ፈረደ በጃዊ ወረዳ የእርሻ ፅ/ቤት ሃላፊና ሌሎችም በርከት ያሉ ስማቸው ያልተገለፁ እንደሚገኙባቸውና አቶ ጌታየ ቢሆነኝ የአንከሻ ወረዳ አስተዳዳሪ፤ አቶ አይተነው ታዴ የጃዊ ወረዳ የእርሻ ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ፤ እቶ አለባቸው የጃዊ ወረዳ የጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሃላፊ የሚገኙባቸው በበጀት አጠቃቀም ችግር ነበራችሁ ተብለው የተገመገሙና በከባድ ማስጠንቀቅያ የታለፉ እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል።