Sunday, September 14, 2014

በሸቀጣ_ሸቀጥ የሚተዳደሩ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ድርጅታቸው በወያኔ ኢህአዴግ ገዥው መደብ እየተወረሰ ኑሮ-አቸውን መምራት እንዳልቻሉ ምንጮቻችን አስታወቁ።



በመቀሌ ከተማ በአደባባይና በአድሓቂ አካባቢ ሆነው ለረጅም አመታት በሸቀጣ ሸቀጥ ስራ ተሰማርተው ሲሰሩ ለነበሩ አነስተኛ ነጋዴዎች የአካባቢው አስተዳዳሪዎች እስካሁን በዝምታ ሲያይዋቸው ቆይተው አሁን ህጋዉያን አይደላችሁም በማለት በማሰር ኑሮአቸውን ይመሩበት የነበረውን ሸቀጣ ሸቀጥ ያልምንም ቅድመ ዝግጅትና ማስጠንቀቂያ በድንገት ስለወረሱባቸው ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
  እነዚህ በአዲሓቂ ሓሸንገ ኮሌጅ አጠገብ የነብሩ ድሓ ባለሱቅ ዜጎቻችንን ነሓሴ 28/2006 ዓ.ም ጥዋት 4፣00 ሰዓት ላይ ፖሊስ ኮምኒቲና የሚሊሻ አባላት በጋራ በመሆን የነበረውን ሱቅ በሙሉ ወረው የወሰዱት ሲሆን ለተወሰኑት የባለሱቅ ነጋዴዎችን ደግሞ ሙላው ወፍጮ ቤት በሚገኘው ፖሊስ ጣብያ ወስደው እንዳሰሯቸው ለማወቅ ትችሏል።