Sunday, September 14, 2014

በሰሜን ጎንደር ዞን በፀገዴ ወረዳ የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል አርሶ አደሮች መካከል ወስጥ ለውስጥ በሚያካሄደው የማናከስ ስራ በሁለቱ ክልሎች አርሶ አደሮች ላይ የሞት አደጋ እያስከተለ እንዳለ ምንጮቻችን አስታወቁ።



ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገለፁት በሰሜን ጎንደር ዞን በፀገዴ ወረዳ ልዩ ስሙ ግጨው በተባለ አካባቢ ነሃሴ 23/ 2006 ዓ,ም ያለ መሬትህ አታርምም በሚል ምክንያት በተፈጠረ ግጭት የአማራ ክልል ተወላጅ የሆነው ሚሊሻ ገረ ዝግሄር ለተባለ የትግራይ ክልል አርሶ አደር በጥይት ተኩሶ የገደለው ሲሆን ይህ ገዳይ ለግዜው የታሰረ ቢሆንም አስፈላጊ የሆነ ምርመራ ሳይደረግለት በአስቸኳይ እንደፈቱት ሊታወቅ ትችሏል።
  ይህንን ድርጊት የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች የወያኔ ኢህአዴግ ቡድን በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተከተለው ያለው ያልተስተካከለ የመሬት አስተዳደር ለግጭቱ መፈጠር ምክንያት እንደሆነና ይህ ተግባር ደግሞ ለስልጣኑ ማራዘሚያ እየተጠቀመበት እንደሚገኝ በመግለጽ በዚህ ያልተስተካከለ የመሬት አስተዳደር ምክንያትም በየጊዜው የብዙ ሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት እየሆነ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ስሜታቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ ለማወቅ ትችሏል።
  ከሰሜን ጎንደር ዞን ሳንወጣ ቃሉ አላዳር የተባለ የፌደራል ፖሊስ አባል አንገረብ እየተባለ በሚጠራው ድልድይ ላይ ነሃሴ 24/2006 ዓ.ም አንድ በንግድ ስራ የምትተዳደር መሰረት ወግአየሁ ለተባለች እንስት የያዘችውን ንብረት ዘርፎ እሷንም በመግደል በአንገረብ ውሃ ውስጥ እንደጣላት ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
   የፈፀመችው በደል ባልነበራት እንስት ላይ አሰቃቂ ግድያ የፈፀመው የወያኔ ኢህአዴግ የፌደራል ፖሊስ አባል እስካሁን በላዩ ላይ ምንም አይነት ህጋዊ እርምጃ እንዳልተወሰደበት ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።