Saturday, October 4, 2014

በአዲስ- አባባ ከተማ የሚኖር ህዝብ ለሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ ከተደረገ በኃላ ለምግብ የማያስፈልግ ነገረወች ዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ ምክንያት ማህበራዊ ንሮውን እንዳይመራ መቸገሩን ተገለፀ።



    በመረጃው መሰረት የአዲስ አበባ ነዋሪ ህዝብ ከስራተኛው ደሞዝ ጭማሪ ተሳስሮ እለታዊ ንሮውን ለመምራት የሚያስፈልጉትን ለምግብ የማያስፈልግ ነገረወች የዋጋ ጭማሪው ከቀን ወደ ቀን እየናረ በመሄዱ የከተማው የገበያ ማእከሎች መረጋጋት ባለመቻላቸው ምክንያትና የሚያስፈልጉትን የምግብ ኣንተወች በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት ስላልቻለ ያጋጠመው ችግር መፍትሄ እንዲደረግለት በማለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት ብሶቱ ቢያቀርብም ተቃውሞ እንድታስነሱ ስለፈለጋችሁ ነው በማለት ደብድበው እንደመለሷቸው ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳመለከተው የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች መጪውን የ2007 ዓ/ም ምርጫ አስመልክተው ቅስቀሳ ለማካሄድ በቦሌ ክፍለ ከተማ፤ አቃቂ፤ ቃሊቲ’ና በሌሎች አካባቢዎች ለሚገኘው ህዝብ መስከረም 8/2007 ዓ/ም በሰበሰቡበት ግዜ ህዝቡ አሁን የሚያስፈልገን ለልጆቻችን የሚሆን ዳቦ እንጅ ስብሰባ እይደለም በማለት ስብሰባውን ለመምራት የመጡትን ካድሬዎች ጥለው እንደሄዱ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።